Anda di halaman 1dari 16

1

የህወሃት ኢህኣደግ ባህርያት ስጋለጥ


ትእዝብቴን ብገልፅስ ቁ.3
ከኣስገደ ገ/ስላሴ ወ/ሚኪካኤል
ከመቀሌ
ይህ ትእዝብቴን ብገልፅስ የሚል ኣርእስት የመረጥኩበት ምክንያት በኣሁኑ ጊዜ በሃገራችን ያለዉ
ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ፣ ማሕበራዊ ችግሮች በየሰኣቱ ፣ በየቀኑ፣ በየሳምንቱ ኣዳዲስ ክስተቶች በፍጥነት
ይታዩና እየተለዋወጡ ስላሉ በተለይ ደግሞ የ ጠ/ሚስቴሩ መለሰ ህልፈተ ህይወት ተከትሎ እየታዩ ያሉት
ክስተቶች በ ህ.ዋ.ሃ.ት ኢ.ህ.ኣ.ደ.ግ መሪዎች እየታዩ ያሉት ጭንቀትና በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለዉ
ጭቆናና ኣፈና ብሎም ኢኮኖማያዊ ብዝበዛ የበረታበት ብሎም በኢትዮጵያ ላሉት ተቃዋሚ ፓርቲና
መሪዎቻቸዉ እንዲሁም የብሄር ብሄረሰቦች ፣ ክልሎች የምንወክል መሪዎች ነን ብለዉ በህጋዊና ሰላማዊ መንገድ
ለሚታገሉ ስም በማጥፋት ወደ ዘረኝነት ፣ ጥላቻ፣ ጭፍን ጠባብነት የሚያመሩ ቅስቀሳዎች በስፋትና በጥልቀት
ዘመቻ የሚካሄዱበት ኣደገኛ ኣዝማሚያ የሚታዩበት ሁኔታ ላይ በመሆናችን ፡

ህዝብ በወታደራዊ ሰንሰለት (ኔት ዎርክ) በመዘርጋት በግድ የሚገዙበት ህዝብ በጭፍን የኮታ ግብር ያለ
ኣግባብ ያለውን ሃብቱ ሟጥጦ ለመንግስት ኣስረክቦ ንግድ ቤቱን ዘግቶ ስደት የሚሰደድበት ሁኔታ ላይ ስላለን
ይባስ ብሎ ኣራት ሚልዮን የትግራይ ህዝብና ኣነስተኛ ነጋዴ ያለበት በብዙ ቢልዮን ግብር ሲከፍል ከ5-30
ሚልዮን ህዝብ ያላቸዉ ክልሎች ኣይከፍሉም ተብለዉ መልኣኩ ፋንታዬ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን
ዳይሬክተር የሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች የፋይናንስና ጉምሩክ ሰራተኞች በየክልላቸዉ ላለዉ ግብር ከፋይ
ህብረተሰብ እንዴት በኮታ ግብር እንደሚወሩት ከትግራይ ክልል የፋይናንስና ጉምሩክ እንዴት ኣድርገዉ ግብር
ከፋዩ ህዝብ እንደሚቀሙት ተሞክሮ( ልምድ) ወስደዉ ተመልሰዉ የኢትዮጵያ ክልሎች ግብር ከፋይ ህብረተሰብ
እንዴት እንደሚቀሙት የተለመደዉ ቅጅ ተሞክሮ( ልምድ) የሚቀስሙበት ጊዜ ስላለን፣ህዝባችን ሁሉም ኣይነት
ኣገልግሎት ለማግኘት ከሚፈለግበት በላይ ግብር እየከፈለ ፀጥታህ ሊጠበቅልህ ከፈለክ የፀጥታ ገንዘብ ክፈል
ተብሎ የሚገደድበት እንዲያውም የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን በማያውቀዉ ሰነድ የሚከፈለዉ ህገወጥ ኣሰራር
የተዘረጋበት ፡

የሃገራችን መሪዎች ከሃገር እስከ ቀጠና ኣስተዳደር ያሉ መሪዎች የራሳቸውን ስራ ሰርተዉ በህዝብ ፊት
ቀርበዉ ሃቁን እንደመናገር ህዝብን በሙታን መናፍስት እንዲመራ በማሰብ ያ “ምርጥ መረያችን”ኣሁንም
በመንፈስ እየመራን ያለዉ ታጋይ መለስ ዜናዊ ነዉ እየተባለ በመፈከር ዘመቻ ህዝብ ወደ ኣልሆነ የመናፍስት
እምነት እንዲጓዝ እንደሚያደርግ ስብከት እምንሰማበት፣የክልላችን መሪዎች በክልሉ ፓርላማ ጉባኤ ለህ.ዋ.ሃ.ት
ኢ.ህ.ኣ.ደ.ግ የሚቃወሙና ግለሰቦች እርምጃ እንደሚወስዱ የሚያስፈራሩበት ፣ መንግስት በሙስሊም ህብረተሰብ
ጣልቃ በመግባት ያልነበረዉ መናጋት በመፍጠርና በሙስሊሙ ህብረተሰብ ቀውሰ በመፍጠር ኣንድነታቸው ላልቶ
እንዲናወጥ የሚያደርግበት ሁኔታ ስላለ እነዚህና እንደነዚህን በመሳሰሉት ኣጀንዳዎች እጅግ ብዙ ስለሆኑ ለነዚህ
ነጥቦችና ተከታትለዉ ለሚከሰቱ ችግሮች ስላሉ እነዚህ ችግሮች ህዝብ ኣውቆ እንዲታገላቸዉ ለማድረግ የመንግስት
2

ብዙሃን መገናኛ ችግሮች በተከሰቱ ጊዜ በየጊዜዉ ለመፃፍ ግልፅ የሆኑ የመንግስትና በየደረጃዉ ለሚገኙ መሪዎችና
ለሚመለከታቸዉ ኣካላት ማጋለጥ ኣይችሉም።

በኣሁኑ ጊዜ ያሉ የግል ጋዜጣ የሚባሉትም ኣብዛኞቹ ፈርተዉ ገባ ወጣ እያሉ ኣንዳንድ ጊዜም የመንግስት
ሚድያዎች እየቀዱየሚዘግቡ በመሆናቸዉ እነዚህም ኣንድ ጊዜ የሚያስፈራሯቸዉ ሲፈልጉም የሚዘጓቸዉ ህዝብ
የሚያስተነፍስባቸዉ የግል ጋዜጣ ሁኔታዎች ሲከሰቱ እንዳንፅፍ እነዛ የሚከሰቱ ችግሮች ፣ መረጃዎች ቶሎ ወደ
ህዝብ ደርሰወዉ ህዝቡ ራሱ እንዲታገላቸዉና ከኣጋሮቹ ጋር ሆኖ ችግሩን ለመቃወም ይችል ዘንድ ብዙ የተለያዩ
ኣጀንዳዎች (ኣርቲስቶች) በኣንድ ጊዜ ለመፃፍ ስለተገደድኩ ኣንባቢያን እንድትረዱልኝ ኣሳስባለሁ።.

በዚህ “ትእዝብቴ ብገልፅስ ” የሚል ፅሁፍ እንደመንደርደርያ የምጠቀመዉ በትግራይ ክልል ያለ


ተጨባጭ ችግር በመዘርዘር ካቀረብኩ በሌሎች ክልሎች ያሉ ችግሮች ተመሳሳይ ስለሆኑ በተጨማሪም ያለኝ
መረጃ በትግራይ እየተፈፀሙ ያሉ ችግሮች ስለሆኑ ነዉ። ነገር ግን በትግራይ ያለ ችግር በሌሎችም የበለጠ
ኣፈናና ሰቆቃ እንዳለ ግን በእርግጠኝነት ለመናገር እችላለሁ። ምክንያቱም ከትጥቅ ትግል ጀምሮ እስከ ኣሁን
በኢትዮጵያ የሚሰሩ ያሉ የሰብኣዊ መብት ጥሰት የመልካም ኣስተዳደርና ፍትህ እጦት የዲሞክራሲና የነፃነት
እጦት በሙሉ በትግራይ ስለሚጀመሩ እንዲሁም በኢትዮጵያ የነበረውና ያለዉ ሁሉም ኣይነት የኣመራር ኣቅጣጫ
ኣፈና በ ህ.ወ.ሃ.ት ጠ/ሚኒስቴር የሚመሩት ማ/ኮሚቴ ከወሰነ ቡኃላም ለሌሎች ክልሎችና የኢ.ህ.ኣ.ደ.ግ ኣባላት
ድርጅቶችና ኣጋሮቻቸዉ መመሪያ ሁኖ ስለሚያልፍ በትግራይ ህዝብ የተወሰነች ሁሉ ፍትህ ይሁን ኣፈና
እንዳለች በኣማራ፣ በኦሮሞ፣ በደቡብ፣ በሶማል፣ በኣፋር፣ በጋምቤላ፣ በጉምዝ ወዘተ ግዴታ መተግበር ኣለበት ሌላዉ
ቀርቶ በኢ.ህ.ኣ.ዴ.ግ ኣባል ድርጅቶችና ኣጋሮቻቸዉ ጉባኤ ሊያደርጉ ከተፈለገ መጀመሪያ የህ.ወ.ሃ.ት ጉባኤ
ይደረግና የሌሎች ፓርቲዎች መሪዎች የህ.ወ.ሃ.ት ጉባኤ ከታዘቡ ቡኋላ በየክልላቸዉ እየሄዱ በህ.ወ.ሃ.ት ፎቶ ኮፒ
(ቅጅ) ጉባኤ ያካሂዳሉ። በነዛ ፓርቲዎች ጉባኤ ጊዜም ከህ.ወ.ሃ.ት ማ/ኮሚቴ ኣማካሪዎች ይላካሉ። እስከ
የጠ/ሚኒስቴሩ ህልፈተ ሞት ጊዜ የነበረዉ ኣሰራር ኢትዮጵያ በህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች ሞግዚትነት ነበር
የምትመራዉ።
ከኣሁን በፊት በተለያዩ የግል ጋዜጦች የውጭ ሬዲዮ ጣቢያዎች (የተለያዩ መድረኮች) እንደገለፅኩት
የትግራይ ህዝብ ለሁሉም ነገር መሞከርያ ስለነበርና ስላለም ህ.ወ.ሃ.ት በትግራይ ፈተና ካለፈ በሌሎች
ክልሎችና ህዝብ ኮፒ ይሆን እንደነበረ የተረጋገጠ
ነዉ ኣሁን በትግራይ ያሉት ችግሮችም እንደተለመደዉ ወደ ሌሎች ክልሎች ኮፒ ሆነዉ እየተሰራጩ ስለሆኑ
በትግራይ ያለ ችግር ብቻ መናገሬ በሌሎች ክለሎችና ህዝቦች ፍትህ፣ ነፃነት፣ ዲሞክራሲና
3

የሰብኣዊ መብት ኣጠባበቅ ፣ ሃቀኛ የህዝብ ልማት ፣ ፍትህና መልካም ኣስተዳደር የህግ የበላይነት መከበር በሽ
ነዉ ማለቴ ኣይደለም በኣንዳንድ ክልሎች እንደ ኦሮሞ ህዝብ የሚያደርገዉ ኣፈና ከትግራይ የባሰ እንደሆነ
እረዳለሁ።

ለሁሉም ነገር ግን ከላይ እንደጠቀስኩት በትግራይ ክልል በህዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለዉ ግፍ በኣርእስት
እየለየሁ ያለዉ መረጃ ለመግለፅ ስለምሞክር ሁሉም የኢትዮጵያ ጭቁን ዜጎች በየኣካባቢያችሁ ወስዳችሁ
ኣንብቡትና ለችግሩ መፍትሄ ክንዳችንና ንፁህ ሃሳባችን ኣስተባብረን በሰላማዊ መንገድ እንታገል።

በትግራይ ክልል ጠባብነት ኣገርሽቶበታል

በትግራይ ክልል በህ.ወ.ሃ.ት የሚመራ ህ.ወ.ሃ.ትና ማለሊት ከ 1967 ዓ/ም ጀምሮ እስከ 1977 ዓ/ም ጠባብነት
የሚባል በሽታ ተጠናውቶበት እንደመጣ የታወቀ እንደነበርና በ1977 ዓ/ም ከ10 ዓመት ቡኋላ የሚለሊትና
የህ.ወ.ሕ.ት ማ/ኮሚቴ ታማኝ ካድሬዎቻቸዉ በጠባብነት ኣስተሳሰብና ተግባር ተበላሽቶ ቆይቶ እያለ በማለሊት
ጉባኤ እንደ ኣጀንዳ ተነስቶ በወቅቱ የኢህድን የኣሁኑ (ብኣዴን) ኣመራርም ስለነበሩ ከ800 በላይ የጉባኤ ተሳታፊ
በነበሩበት ውይይቱ ተጧጥፎ ህ.ወ.ሃ.ት ጠባብነት የተጠናወተዉ ድርጅት ነበር የሚልየሞቀ ክርክር በመቶ
የሚቆጠሩ የህ.ወ.ሃ.ት ካድሬዎችና ከስድስት በላይ የባኣዴን ማ/ኮሚቴ ኣቋም ይዘዉ ጠንክረዉ በመከራከር
ህ.ወ.ሃ.ት ጠባብ ነበረ ለዚህም እንደ ማስረጃ በፕሮግራም (ማኒፌስቶ) በኣማርኛ ፣ በትግርኛ፣ እንግሊዝኛ የተፃፈዉ
በመላዉ ኣለም የተበተነዉ የትግራይ ትግል ከቅኝ ገዢዋ ኢትዮጵያ (ኣማራ) ነፃ ለመውጣትና ነፃ ሃገር
ለመመስረት ነዉ የሚል ነበር ብለዉ ተከራከሩ ለዚሁ ግንባር ቀደም ፀረ ጠባብነት አቋም ይዞ የተከራከረ ሃይለ
ጥላሁን ( የኣሁኑ ከ ኢ.ህ.ኣ.ዴ.ግ ሰራዊት የተቀነሰዉ ጀነራል ሃይለ ነበር ዛሬ ድምፁ ቢያጠፋም ሃይለ ለ
ህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች ታላቅ ተከራካሪ ነበር ሃይለ በህ.ወ.ሃ.ት የትምክህት ወኪል ነዉ የሚባል ስም የነበረዉ እንደ ዛሬ
ድምፁ ፀጥ ያለ ኣልነበረም።

በወቅቱ የነበረዉ የ ህ.ወ.ሃ.ት ማ/ኮሚቴ ግን የነበረዉ የጠባብነት ኣቋም በፈጠረዉ ችግር ብዙ የፖለቲካ
ፓርቲዎች ኢ.ህ.ኣ.ፓ ጨምሮ ኣጥፍቶ እያለ በጉባኤ የቀረበለት ሂስ ኣሜን ብሎ ከመቀበል በመግደርደር ኣዎን
ሙሉ በሙሉ ጠባብነት ነበረን ብለን ባንቀበልም በዝንባሌ ደረጃ ግን ነበርን ምክንያቱም የጠባብነት ኣቋማችን በ6
ወር ውስጥ ኣስተካክለናል ያሉት እኔ እስከማውቀዉ እስከ 1977 ዓ/ም በስብሰባ፣ በመፅሄት ፣ በኮንፍረንስ ፣
በሁለት ጉባኤዎች በካድሬ ትምህርት ቤት ተነስቶና ተነጋግረንበት ኣናውቅም እስከ ኣሁንም ህ.ወ.ሃ.ት ጠባብ
እንደነበረ እንዳልሆነና በዝንባሌ ብቻ ትንሽ ጠባብነት ነበረኝ በማለት ነዉ የሚናገረዉ።
4

ከ1983 ዓ/ም ቡኋላም ለ ህ.ወ.ሃ.ት ኢ.ህ.ኣ.ዴ.ግ የሚቃወሙ ሃገር ኣቀፍ ክልላዊ ብሄራዊ ፓርቲ የነበሩና ኣዲስ
የተፈጠሩ ፓርቲዎች ለ ህ.ወ.ሃ.ት ኢ.ህ.ኣ.ዴ.ግ ፓርቲ ፊት ለፊት መቃወም ሲጀምሩ በኣንድ በኩል
ዲሞክራሲያዊ ህግ-መንግስት ኣፅድቀናል በኢትዮጵያ መድበለ ፓርቲ እንዲኖር ፈቅደናል በሰላማዊ መንገድ ህገ-
መንግስትን ኣክብረዉ ለሚታገሉ የምርጫ ሃይሎች መጫወቻ ሜዳ ፈጥረናል ብለውን ነበር ህ.ወ.ሃ.ት
ኢ.ህ.ኣ.ዴ.ጎች በሌላ ኣቅጣጫ ህ.ወ.ሃ.ት ራሱ የስራው ኣባል ድርጅትና ኣጋሮቹ ( የራሱ ሎሌዎች) ያደረጋቸዉ
ካልሆነ ለህ.ወ.ሃ.ት ፖለቲካዊ እምነት ፖሊሲ ሁሉ ኣቀፍ ኣስተሳሰብ የማይቀበሉ የሚቃወሙ ፓርቲዎች የጠባብ፣
የትምክህት፣ የመሳፍንቶች የሚሉ ስም በመለጠፍ እንደልማዱ ለኢ.ህ.ኣ.ፓ ፣ ኢ.ድ.ዩ ጠርናፊት ግንባር ፣ ገድለ
ትግራይ ወዘተ በነፍጥ እንደኣከሰማቸዉ ሁሉ ለነዛ 1983 የተፈጠሩ ፖለቲካዊ ፓርቲዎችም በተለያዩ ተንኮልና
ሴራ ኣከሰማቸዉ። ኣሁንም በተጨማሪ የተለያዩ ሃገራዊና ክልላዊ ፓርቲ በብሄራዊ ፓርቲ ተፈጥረዉ ህገ
መንግስት ኣክብረዉ ጠንክረዉ በሚታገሉ የኣሸባሪ መዋቅር የትምክህትና የጠባብ ሃይሎች በሻዕብያ ኣስተባባሪነት
በኣልሸባብ ደጋፊነት ጎን ተሰልፈዉ ኣገር የሚጎዱ በማለት ለእስር ለእንግልት ለግርፊያ (ቶርች) ሰለባ በመሆን
በኣስር የሚቆጠር ኣመታት እድሜ ይፍታህ እስራት እንዲዳረጉ ተደርጓል ሩቅ ሳንሄድ በኦሮሞ በአማራ ትግራይ
በደቡብ በሌሎች ክልሎች በሺ የሚቆጠሩ የሰላማዊ ተቀዋሚ ፓርቲ ኣባላት የተለያዩ ከባድ ቅጣት የደረሳቸዉ
ባልታወቁ ታጠቂዎች መንግስት ባለበት ኣገር የተገደሉ እንተወውና በቅርብ ጊዜ የእነ በቀለ ግርሙ ኣንዱ ኣለን
ኣራጌ እስከዳር ሌሎች በመድረክ ኣባላትና ጋዜጠኞች በኣሸባሪነት በመፈረጅ እየተሰቃዩ መሆናቸዉ ሁሉ
ኢትዮጵያዊ ዜጋ በቅርብ የሚከታተለዉ ያለዉ ነዉ። ህ.ወ.ሃ.ት ከ1967 ዓ/ም እስከለ ቅርብ ጊዜ የኢትዮጵያ የነበሩ
የተለያዩ ኣመለካከት ይዘዉ ለትግል የተሰማ በውውይት እንደመፍታት ፈንታ በነፍጥ በእስራት ካገር በመበታተን
እያወጣቸዉ እንደመጣ የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነዉ። እንዴት እንዳወጣቸዉ ለመተንተን በዚች ኣጭር ፅሁፍ
ለመግለፅ ኣይቻልም። ለታሪክ ፀሃፊዎች ልተወዉ ታሪክ ፀሃፊዎች ይመራመሩበት።

እሚብሰዉ ግን ህ.ዋ.ሃ.ት ኢ.ህ.ኣ.ደ.ግ በኢትዮጵያ ያለ ዲሞክራሲ ተወዳዳሪ የሌለዉ ዲሞክራሲ ኣለ ምርጫ


2002 99.6% ኣሸነፍኩ እያለ የሚመፃደቅበት ወቅት በኣሁን ጊዜ ያ የነበረ ጠባብነትና ዘረኝነት ኣገርሽቶበት
ከክልል ፣ ዞን፣ ወረዳ፣ ቀበሌ፣ በመጨረሻ ጥቅምት ወር ኮምፈረንስ ሲካሄድ ሰንብተዋል።

ኮምፈረንሱ ከ3 ቀን እስከ 4ቀን የፈጀ ነበር ከዛ በፊትም ከ1.3ሚልዮን በላይ የሚሆን ህዝብ ለልማት ነዉ በሚል
ሽፋን ከ5-7ቀን የፈጀ ስብሰባ ነበር። በነዚህ ኮምፈረንስና ስብሰባዎች የነበረ ኣጀንዳ ለትግራይ ህዝብ ሰበካ
ሲሰብኩ እነ ስዬ ኣብርሃ ፣ ገብሩ ኣስራት፣ መራራ ጉዲና የትግራይ ህዝብ ጠላቶች የጠባብና ትምክህት ሃይሎች
እንደዲሁም የጥፋት ሃይሎች ይዘዉ መጡ በማለት የኮምፈረንስ ተሳታፊ ህዝብና ካድሬ በጠባብነት ሙዚቃ
ሲንቀሳቀሱ ሰንብተዋል ። ዓረና መድረክ የጥፋት ሃይል ነዉ ኣስፈላጊ እርምጃ እንወስዳለን ሲሉ የክልሉ ቁንጮ
ኣባይ ወልዱ ሳይቀሩ የኣንባ ገነን ዲስኩራቸዉ ሲያሰሙ ሰንብተዋል። በዚህ ኮምፈረንሶች የእድሜ ባለፀጋ
ሽማግሌዎች ሳይቀሩ ተቀሰቀሱ ሐዚ’ውን እቲ ብሉፅ መራሒና ብመንፈስ ዝመርሐና ዘሎ ተጋዳላይ መለስ
ዜናዊ እዩ(ኣሁንም ያ የበለጠ መሪያችን በመንፈስ የሚመራን ያለዉ ታጋይ መለስ ዜናዊ ነዉ) የሚል መፈክር
ያለዉ ማስገደጃ ደብዳቤ እየተሰጣቸዉ ነበር የተሰበሰቡት ። ስብሰባዉ በሁሉም ኮንፍረንስ ፕሮፌሰር መራራ
5

ጉዴና ኣቶ ቡልቻ ዲመክሳ ዶክተር ሃይሉ ኣርአያ ፕሮፌሰር በየነ ፔጥሮስ ሌሎቹም የጥፋት ሃይሎች እየተባሉ
ሰንብተዋል መድረክ የጥፋት ሃይል የኢ.ህ.ኣ.ደ.ግ ኣንድነት ለመበታተን ሰላማዊ መስሎ በውስጣችን ገብቶ
ለማበላሸት ገብተዋል እንጠንቀቅ ሲባል ሰንብተዋል ይህ የሚሆነዉ ለምንድነዉ ? እነ ፕሮፌሰር ምን ኣደረጉ
21ዓመት ሙሉ በኢትዮጵያ መድረክ ቆመዉ ለኢትዮጵያ ሉኣላዊነት ነፃነት የባህር በር ሲታገሉ የቆዩ ናቸዉ ።

መድረክስ ምንድነዉ የሚባለዉ ያለዉ በሻዕቢያ ኣስተባባሪነት በኣሸባሪዎች ደጋፊነት የሚንቀሳቀስ ተብሎ
ይወነጀላል። እንዴት ብሎ በየትኛዉ መመዘኛ ? እኔ እንደሚገባኝ መድረክ የሚባለዉ የኢትዮጵያ ኣንድነትና
እኩልነት ይኑር የኢትዮጵያ ሉኣላዊነት ይከበር ኢትዮጵያ የባህር በር ባለንብረት ናት የኣርጀርስ ስምምነት
መቀበል ኣገራችን መሸጥ ነዉ እያሉን ያሉት ታዲያ ከሻዕቢያ በምን ይዛመዳል? ይህ ኣባባል ሊበሏት የፈለጉ
ኣሞራ ጅግራ ይሏታል እንደማለት ነዉ። ኢ.ህ.ኣ.ደ.ግ ኣሁንም ለ38 ኣመት ሙሉ እየዋጣቸዉ እንደመጣ
መድረክና ተመሳሳይ ፓርቲዎች እንደልማዱ ሊውጠዉ ስለፈለገ ነዉ። ግን ደግሞ ኣይቻልም ጊዜዉ 21ኛ ክፍለ
ዘመን ስለሆነ የኢትዮጵያ ህዝብ ከኢ.ህ.ኣ.ደ.ግ ፊት ሄዶ ስለተራመደ ኣሁን ጠባብነት ቦታ የለዉም ።
መድረክ ከሻዕቢያ ሊስማማና ሊተጋገዝ ይችላል ተብሎ ኣይታማም ይልቁን ህ.ወ.ሃ.ት ኢ.ህ.ኣ.ደ.ግ ራሱን ይፈትሽ
ይታማል ብቻ ሳይሆን ውስጡ የኤርትራውያን መናሃርያ ነዉ።

ኣንድ ጥያቄ ላንሳ ህ.ወ.ሃ.ት እንደ ሃይሉ ኣርአያ ፕ/በየነ ፕ/መራራ ሌሎችም የኢሰፓ ወንጀለኞች ናቸዉ በማለት
21 ኣመት ሙሉ እየወነጀሏቸዉ ቆይተዋል በበኩሌ ምናልባት ዶክተር ሃይሉ ኣርአያ ይኖሩ ይሆናል ሌሎች ግን
ኣልነበሩም ። ቢኖሩስ ከደርግ ጋር የነበረ ሁሉ ወንጀለኛ ነዉ?
ሌላ ጥያቄ ኣለኝ እነ ዶክተር ንዋዩገብረኣብ ዶክተር ኣድሃና ሃይለ፣ ኣቶ መኮነን ኣብርሃ ሌሎች ከፍተኛና
መካከለኛ መኮንኖች ምርኮኞች ሳይቀሩ የ ህ.ወ.ሃ.ት ኢ.ህ.ኣ.ደ.ግ ከፍተኛ ኣመራር ደርሷል ኣሁንም ቁልፍ
ቦታ ይዘዋል ። እነዚህ ያለፉ ስርዓቶች ተገደዉ ይሁን በፍላጎታቸዉ የስርዓቱ ኣገልጋይ ሆነዉ ቀይቷል። በበኩሌ
በሁሉም ጎራ ያሉት ባለስልጣኖች ባላቸዉ ሞያ ለሃገራቸዉ ቢሰሩ ተቃውሞ ኣልነበረኝም ኣሁንም የለኝም ግን
እነዚህ በደርግ ዘመን ባለስልጣን የነበሩ ወደ ህ.ወ.ህ.ት ሲሰለፉ መላእክት ወደተቃውሞ ወገን ሲሰለፉ ሰይጣናት
ብሎ ማነዉ የሰየማቸዉ።

እዚህ ላይ ህ.ወ.ህ.ት ኣሁንም የ1983 ዓ/ም ስህተት ኣልበቃ ብሎት በደርግ ስርዓት የነበረ በሃገር መከላከያ ሰራዊት
ምድር ሃይል ፣ የኣየር ሃይል፣ የባህር ሃይል፣ ፖሊስ፣ ድህንነት፣ የሲቪል ባለሙያ ዜጎች የኣሜሪካ፣ የኣውሮፓ፣
የኤስያና ሌሎች ኣገሮች ሳይንስ የቀሰሙ የኢትዮጵያ ሃብት የፈሰሰባቸዉ ዜጎች ኣጠናክሮ እንደ መለስን
በመቃወም የሃገር መከላከያ ሃይል እንድናጣና ብዙዎች እንደንፋስ ሲበተኑ በሺ የሚቆጠሩ የጦር መኮንኖች አየር
ሃይል ፓይለቶች መካኒኮች የባህር ኣዛዦች በእስር ቤት በማጎር የ60 ኣመት ልምድ ያላቸዉ ዜጎች መበተኑ
6

በሻዕቢያ ወረራ ያጋጠማቸዉ ችግርና የሳይንስ ጉድለት በፈጠረዉ ውድቀት ተረድቶት ወደኋላ ተመልሶ ያስብ
እንደነበረ ኣድርጌ እገምት ነበር ግን ግምቴ ስህተት ነበር ምክንያቱም ህ.ወ.ህ.ት ኣሁንም ከ21 ኣመት ቡኋላ
ኢሰፓ የጥፋት ሃይል እያለ መዘመሩ ያሳዝናል። ለመሆኑ ከነሱ ጋር ያሉ ምን ይሉናል ኣይሉም ሰዎች
ኣይደሉም? ሌላ ጥያቄ የኦሮሞ የኣማራና የደቡብ የትግራይ ሰላማዊ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጠባቦችና በትምክህት
ኢሰፓ የጥፋት ሃይሎች ካላቸዉ ለትግራይ ህዝብም ከነዚህ 80 ሚሊዮን ህዝብ ካጣላዉ የትግራይ ህዝብ መዓት
ነዉ የሚጠጋዉ?

ኣንዳንድ ጊዜ የ ህ.ዋ.ህ.ት መሪዎች የሚናገሩት ስሰማ ከ38 ኣመት በፊት እነ ወልደኣብ ወልደማርያም ኤርትራ
ትግራይ ኣፋር በመያዝ ወልቃይት ፀገዴ ፀለምት ወልዲያ ተከትላ ቀይ ባህር በሙሉ በመቆጣጠር ጠንካራ
የሰሜን ኢትዮጵያ መንግስት መመስረት የሚል ህልማቸዉ የሚደግፉ ዜጎች እንዳይኖሩ እጠራጠራለሁ በ
ህ.ዋ.ህ.ት መሪዎች ከዚህ ጉዳይ ንፁህ ናችሁ በሚል ሃሳብ በጭንቅላቴ ይጉላላል። ምክንያቱም ህ.ዋ.ህ.ት ከጅምሩ
የሻዕቢያ ኣቅጣጫ ተከትሎ ምንም ታሪካዊ ተያያዥነት የሌለዉ ትግራይ ነፃ ሪፐፕሊክ (ነፃ ሃገር) ከሚል ጠባብነት
ኣቋም ሳያይዘዉ ሃቅ ይሆናል።

በሌላ በኩል የመድረክ ኣመራር በተለይ ደግሞ የዓረና ኣመራር እነ ኣቶ ገብሩ ኣስራት ኣሜሪካ ሂደዉ በዊስኪ
እየታጠቡ ከጠላቶቻን ከነ ኢ.ህ.ኣ.ፓ. ጋር ታርቀዉ ጠላቶች ይዘውልህ እየመጡ ነዉ ተዘጋጅ ብለዋል
የትግራይ ክልል መሪዎች በሁሉም ኮንፍረንሶችም ኣጀንዳ ነበር። ዊስኪ መጠጣቱ ማነዉ የሚታማዉ ብሎልበል
በ10,000፣ 50,000፣ 30,000 ብር በመግዛት ቻፓይዝና ብላክ ለበል እንደ ውሃ የሚታጠበዉ ማነዉ? ሰማይ ጠቀስ
ህንፃዎች የሰሩ እነማናቸዉ የኢትዮጵያ ህዝብ መስተዋት ነውና ራሱ ይመስክር ።

ሌላ ከኢ.ህ.ኣ.ፓ ጋር ታርቀዉ ጠላትን ይዘውልህ ይመጣሉ ተብሎ ህዝብ ላይ ሽብር ተዘርግቷል ከኢ.ህ.ኣ.ፓ
ጋር ምን የሚያጣላ ነገር ኣለ ተስማምተዉ በሰላማዊ መንገድ ቢታገሉና ቢስማሙ ምን ችግር ኣለዉ። ኢ.ህ.ኣ.ፓ
እኮ የኢትዮጵያ ኣብዮት የወለደዉ ነዉ።ህ.ዋ.ህ.ት እነደሆነ በ ህ.ዋ.ህ.ት ሳንባ ያልተነፈሰ በጠላትነት መፈረጅ
ከጥንቱ ይዞት የመጣ ባህል ነዉ። ይህ ቂም በቀል ለትውልድ ሊያወርሱት ነዉ? ኣሁን እኮ እኛ የእድሜ በላፀጎች
ነን ለምን ቂም በቀል እርግፍ ኣድርገን ትተን ለትውልድ ጥሩ ጥሩውን ኣናስተምረውም።የትግራይ ክልል
መሪዎች ኣጉል ስጋትና ጭንቀት የፈጠረዉ ነዉ መሰለኝ የዓረና ትግራይ ፓርቲ ኣቶ ስዬ ኣብርሃ እና ኣቶ ገብሩ
ኣስራት የትግራይ ህዝብ ጠላቶች መሳሪያ ሆነዋል በማለት ትልቅ የስም ማጥፋት ዘመቻ ያካሂዳሉ።በኔ እምነት
ኣቶ ገብሩና ኣቶ ስዬ ኣብርሃ የህ.ዋ.ሃ.ትን ፀረ ዲሞክራሲ ሰንሰለት በጥሰዉ በመውጣት በተቃውሞ ዲሞክራሲ
መግባታቸዉ የነበራቸዉን የኣመራር ልምድ ለዚህ ኣዲስ ትውልድ ለማውረስ በመቻላቸዉ ምስጋና ይገባቸዋል።
የህ.ዋ.ሃ.ት ኣመራር የሚያስጨንቀዉ ምክንያት የበታችነት ስሜትና በራስ ኣለመተማመናቸዉ የመነጨ ነዉ።

እነ ኣቶ ገብሩ ኣስራት ሊያመጡት የሚችሉ ሃይል ወዳጅ እንጂ ጠላት ኣያመጡም የሚያመጡት የትግራይ ኣካል
የሆነ ኣማራ፣ኦሮሞ፣ ጉራጌ፣ ሶማል፣ ኣፋር፣ሃደሬ፣ጋምቤ፣ኣኝዋክ፣ ከንባታና ሃዲያ ወዘተ ነዉ የሚያመጡት የኢሳያስ
7

ወረራ ኣያመጡም በዚህ ኣይታሙም መድረክ በመሰረ ቱ ህ.ወ.ሃ.ት በየጊዜዉ ኮትኩቶ እሚያሳድገዉ ጠባብነትን
በመቃወም ለኢትዮጵያ ህዝቦች ኣንድነትና እኩልነት ሉኣላዊነት ስለሚታገል ለ ህ.ዋ.ሃ.ት መሪዎች እንደ እሳት
ስለሚያቃጥላቸዉ ነው።

ኣንድ ጥያቄ ለህ.ዋ.ሃ.ት መሪዎች ልጠይቃቸዉ ለመሆኑ ሩቅ ሳንሄድ በጥቅምት ወር 2005 ዓ/ም የኣሜሪካ
ፓርላማ ውድድር ሲካሄድ ሰንብቷል ኣለማችን በምሳሌነት ያደነቀዉ ውድድር ኣንደኛ በቅስቀሳ ወቅት ሁለቱም
ተወዳዳሪዎች ፊት ለፊት በህዝብ ፊት ቀርበዉ ሲከራከሩ ህዝብም ነፃ ሆኖ ሲጠይቅ ኣስተያየት ሲሰጥ የሃገሪቱ
የመንግስትና ብዙሃን መገናኛ ለሁሉም ተወዳዳሪዎች እኩል ሲያገለግሉ የፖሊስ፣ የቀበሌ፣ የወረዳ ፣የዞን የክልል
ኣስተዳዳሪዎችም ጣልቃ ሳይገቡ ተወዳዳሪዎቹ ኣንገት ለኣንገት ተቃቅፈዉ ሲለያዩ ለጥቁር የኣፍሪካ ኣፋኞች
የኣፍሪካ መሪዎች ምን ያህል ኣስተማሪ መሆኑ በተለይ 21 ኣመት ሙሉ በምርጫ ውድድር ያጭበረበረዉ
የህ.ዋ.ሃ.ት መንግስት ሊማርበት በቻለ ነበር።

የኣሜሪካ ተወዳዳሪዎች በሃገር ኢኮኖሚ ፖሊሲ በማህበራዊ በውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ሲከራከር በተለይ ኣሁን
ባለዉ የኣሜሪካ የኢኮኖሚ ቀውስ እንዴት መፍትሄ እንደሚሰጡት ሲከራከሩ በሁሉም ተወዳዳሪዎች ኣንድም
የስድብና የመናናቅ ዝንባሌ ኣልታዩም። ህዝቡም የሁሉም ተወዳዳሪዎች ክርክር ኣስተሳሰብና እምነቶች በክርክሩ
ወቅት በቂ ግንዛቤ በመውሰድ ካርዱ ለማን እንደሚሰጥ ግንዛቤ ኣግኝተዋል።ተወዳዳሪዎችከ400 ሚሊዮን በላይ
የኣሜሪካ ህዝብ ልብ ውስጥ በመግባት ለምርጫ ቀረቡ በምርጫዉ ወቅትም እንደ ህ.ወ.ሃ.ት መንደር የሚያደርገዉ
ምርጫ ሳይሆን በሁሉም የምርጫ ሳጥን የቀበሌ፣ የቀጠናሴቶች ኣይታዩም የምልሻ ኣጋፋሪ የኣንድ ፓርቲ
ህዋሳቶች ፖሊስ የኣንድ ፓርቲ ኣጫፋሪዎች የወረዳ፣ የቀበሌ መሪዎች ኣይታዩም ህዝቡ ነፃ ሁኖ መርጦ ይሄዳል
ምርጫ ካለቀ ቡኋላ እንደ ኣገራችን ምርጫ ኮሮጆዎች ሲሰረቁ ሰዉ ሲታሰር ሲገደልኣልታየም የምርጫ ኣፈፃፀም
ግልፅና በህግ ስለተፈፀመ ለቆጠራዉ ጊዜ ሳይወስድ ማን ኣሸነፈ ለማወቅ ጊዜ ኣይወስድም። የምርጫዉ ሂደት
ይቅርና ለኣሜሪካኖች ለመላዉ ለኣለም ህዝብ ግልፅ ነበር።

የኣሜሪካ ተወዳደሪዎች በኬኒያ ኣሜሪካዊና በነጭ ኣሜሪካዊ መካከል ነበሩ። በነዚህ ተወዳዳሪዎች የዘር፣
የሃይማኖት የቀለም ልዩነት በህዝቡም በኣሜሪካ ባለስልጣኖች ኣልታዩም የኣብዛኞቹ ነጮች ኣገር የሆነች ኣሜሪካ
ኣንድ ጥቁር ኣፍሪካዊ ከ400 በላይ የኣሜሪካ ህዝብ ለ8 ኣመት ስልጣን ሲይዝ የዘርና የቀለም ልዩነት የሰለጠኑ
ኣግሮች እንዴት እንዳጠፉት ለጥቁር የኣፍሪካ መሪዎች ብቻ ሳይሆን ለህዝብም ትልቅ ትምህርት ነዉ።የህ.ወ.ሃ.ት
ኢ.ህ.ኣ.ደ.ግ መሪዎች ግን እንደነ ኦባማ በፖለቲካ በኢኮኖሚ ፖሊሲ በኣገር ውስጥና በውጭ ፖሊሲ ማእከል
ኣድርገዉ ተወዳድረዉ ህዝብ ኣሳምነዉ ህዝቡም በነፃ ሃሳቡን እንዲገልፅ ግልፅነትና ተጠያቂነት ባለበት ሁሉም
ሚድያ ለሁሉም ሃይሎች እኩል ንዲያገለግሉ በማድረግ በፍትህ ኣካላት በሚሳተፍበት ምርጫ እንዲፈፀም
እንደማድረግ ፋንታ ተወዳዳሪዎችን ማሰር ማንገላታት መግደል ደጋፊዎቻቸውን ማሰር ከህብረተሰቡ እንዲገለሊ
ማድረግ ለፖለቲካ መሪዎች መስደብ ማዋከብ ህዝቡን በጠባብነትና በዘረኝነት መቀስቀስ ከምርጫ ቦርድ መዋቅር
ጀምሮ የኣስመራጭ ኣካላት ገለልተኛ ኣለመሆናቸዉ ሁሉም የሚሰሩ ስራዎች ህገ መንግስቱን እንኳን ኣክብሮ
8

በመሄድ ፋንታ ህግመንግስቱን በመናድ ሁኔታውን ያበላሸዋል ። በኣገራችን የተካሄዱ ምርጫዎች በሙሉ በ
ህ.ዋ.ህ.ት ኢ.ህ.ኣ.ደ.ግ ፈላጭ ቆራጭነት የተፈፀሙ ነበሩ።ህ.ወ.ሃ.ት እንዴት ብሎ ከነ ኣሜሪካ ጋር ይወዳደራል
ኣሁንም እየደገመዉ ነዉ በትግራይ ያለዉ 4.3 ሚሊዮን ህዝብ ከ ህ.ዋ.ህ.ት ውጭ ሌላ ኣታምልክ እየተባለ
ይገደዳል ሁሉም እንቅስቃሴ በስለላ መዋቅር ተወጥሯል ከላይ እንደገለፅኩት በኔት ዎርክ ተወጥሯ በ ህ.ዋ.ህ.ት
ከጅምሩ ከጠባብ ኣመለካከቱና እምነት ተነስቶ በኢትዮጵያ የነበሩ ፀረ ደርግ ሃይሎች ቡኋላም ለህ.ወ.ሃ.ት
ኢ.ህ.ኣ.ደ.ግ የሚቃወም ፖለቲካ ፓርቲዎች ለኣብዛኞቹ በጦርነት ቀላል የማይባሉ ፓርቲዎች ደግሞ በተለያየ
መንገድ ያከሰመ ፓርቲ ነዉ። ህ.ወ.ሃ.ት ያጠፋቸዉ ፓርቲዎች ለመጥቀስ ስለሆነም ጠባብነት በትግራይ እንደ
ኣዲስ ኣገርሽቶበታል ማለቴ ትክክል ነዉ። በኣጠቃላይ ህ.ዋ.ህ.ት ከኣሜሪካ የምርጫ ውድድር ሊማር የማይችል
ፓርቲ ነዉ ምክንያቱም ኣይቀሰቅሱም ነበር
1. ከጅምሩ ትግራይ ገድለ ሓርነት
2. ጠርናፊት
3. ኢድዩ
4. ኢ.ህ.ኣ.ፓ
5. በ1970፣በ1972፣በ1984 ዓ/ም
6. ኦነግ
7. በሶማልና በደቡብ የነበሩ ፓርቲዎች በውጊያ ኣክስሟቸዋል።
2. በሰላም ህገ-መንግሰት ኣክብረዉ ለሚታገሉም ሆን ብሎ መሰናክል በመፍጠር ያልሆነ ምክንያት ታስረዋል
እየታሰሩም ነዉ። ከኣገር ወጥተዉ በስደት የመከራ ኑሮ እየገፉ ይኖራሉ ለነዚህ የትምህክትና የጠባብ ሃይሎች
እያሉ ይወነጅሏቸዉ ነበር ኣሁንም በተጠናከረ መልኩ እየቀጠሉበት ይታያል ህ.ዋ.ህ.ት ግን በጠባብነትና
ትምክህት ስሜትና ኣመለካከት የላሸቀና ፍፁም ሊሻሻል የማይችልበት ሁኔታ እየተፈጠረ ነዉ።

ምክንያቱም በኣሁኑ ጊዜ በትግራይ ክልል የሚታየዉ የጠባብነት ቅስቀሳ በተጨባጭ እያየነዉ ነዉ። ከላይ
የጠቀስኳቸዉ ፓርቲዎች ያጠፏቸዉ (ያከሰሟቸዉ) ከጠባብና ትምክህት ኣመለካከት ተነስቶ ነዉ የፈፀመዉ
ስለሆነ የጠባብነት የትምክህት ኮር የህ.ዋ.ሃ.ት መሪዎች ናቸዉ ለማንም እሚለጠፍ ስምና ተግባር ኣይደለም።
ለምን በሙታን መናፍስት እንመራለን ጠ/ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ ለህ.ዋ.ህ.ት ኢ.ህ.ኣ.ዴ.ግ በቁንጮነት ከመሩ
እነሆ ከ1982 ታህሳስ ወር እስከ 2004 መጨረሻ ኣመት ለ22ዓመት ሙሉ በህይወት መርተዋል ።

በህይወት በነበሩበት ዘመን ሃገራችን በጠንካራ ጎንም ሆነ በደካማ ጎን በዲሞክራሲ ፀረ ዲሞክራሲን በተዘበራረቀ
መንገድ እየመሩ ቆይተዉ በ2004 መጨረሻ ኣመት ኣካባቢ ከዚህ ኣለም በሞት ተለይተዋለ። ከሳቸዉ ሞት ጋር
ተያይዞ ስለ ጠ/ሚኒስቴሩ ብዙ ተብለዋል የ ኢ.ህ.ኣ.ዴ.ግ መሪዎችና ካድሬዎች የ ህ.ዋ.ህ.ት ታጋይ ብዙ
ተናግረዋል ኣልቅሰዋል በትእዝብቴን ብገልፅስ ቁ.1 ፅሁፍ ላይ እንደገለፅኩት 80 ሚልዮን የኢትዮጵያ ህዝብ
እድሜዉ የደረሰ ሁሉ በነቂስ ተሰባስቦ ኣደባባይ ወጥቷል። ኣልቅሷል ይህ ሃዘንና ከልብ የነቀለ /ከኣንገት በላይ/
ለሚለዉ የሚያውቀዉ 2ኣልቃሻዉ
9

ከያኒዉ ገጠጣሚዉ ራሱ ያውቀዋል በበኩሌ ለጠ/ሚኒስቴር ሃዘን መደረጉ እንደ ዜጋም እንደ መሪም ምንም
ኣለኣስፈላጊ ኣንጡራ ሃብት የባከነ ቢሆን ማዘኑ ተገቢ ነበር። ሁላችንም ኣዝነናል ስርኣታቸውን እንቃወማለን
እንጂ የሳቸዉ ክፉ ነገር ኣንመኝም ነበር። ግን ደግሞ እንደመናፍስት አላመለክንም ። በ ህ.ዋ.ህ.ት የትጥቅ
ትግል ጊዜ በደርግና በተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ በተደረገዉ ጦርነት በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ጀግኖች ታጋዮች የገጠር
ምልሻ የከተማ ካድሬዎች ለጠ/ሚኒስቴር መለስ ይመሩ የነበሩም ሞተዋል በቅርብ እንኳን የ ኢ.ህ.ኣ.ደ.ግ ኣይንና
ፈላስፎች የነበሩ ጀነራል ሓየሎም ኣርአያ ፣ ጀነራል በርሀ ወ/ጅወርግስ ሞተዋል እነዚህ በቅርቡ መሪዎች
የሰራዊታችን የህዝባችን ኣለኝታ የሆኑ ጓዶች በሞሞታቸዉ ኣዝነናን ኣልቅሰናል ሆኖም ግን እንደ መናፍስት
ከኣምላክ በላይ ኣላመለክንም።

ይህ እንዳለ ሆኖ ግን ጠ/ሚኒስቴር በመሞታቸዉ ኣሳዛኝ ሆኖ እንሰ መናፍስት ማምለክ ኣይገባም። ይህ ያልኩበት


ምክንያት በኣሁኑ ጊዜ የ ህ.ዋ.ሃ.ት መሪዎች ስለ ጠ/ሚኒስቴር በሚመለከት ወደ ህብረተሰቡ ያልሆነ ህሊናዊ
(ኣይዲያሊስት) ኣስተሳሰብ እያስተላለፉ ይገኛሉ ይህም ኣንድ ሰዉ ከዚህ ኣለም በሞት ከተለየ ወደ ኣፈር
ተቀይሯል ስራዉ ሁሉ በሂወቱ እያለ በጎም ይሁን መጥፎ ሰርቶ ኣልፏል ታሪኩ ብቻ ይኖራል ታሪኩ በበጎም
በመጥፎም የሰራቸዉ ተግባራት ሁሉም ለህብረተሰቡ በሁሉም መልኩ ትምህርት ናቸዉ። ሃቁ እንደዚህ እያለ ግን
የህ.ዋ.ሃ.ት መሪዎችና ኣጋራቸዉ የሆኑ የፓርቲ መሪዎች እንደ ብኣዴን፣ ኦህዴድ፣ ደቡብ፣ ሌሎችም መሪዎች
ማለቴ ነዉ በራሳቸዉ ኣቅም ሰርተዉ ማንነታቸዉ እንደማሳወቅ በህይወት በሌሉ ጠ/ሚኒስቴር መናፍስት ሆነዉ
እንደጌታ እየሱስ ክርስቶስ ተሰቅሎ ሞቶ በእጊኣብሄር ፍቃድ ትንሳኤ ሙታን ሆኖ እንደተነሳ እየተጠበቅን እንዳለ
እንደምናምነዉ ሁሉ ኣሁን ደግሞ እያሉን ያሉት ምርጥ መሪያችን ኣሁንም በመናፍስት እየመራንያለዉ ታጋይ
መለስ ዜናዊ ነዉ ይሉናል ቃል በቃል በትግርኛ የተፃፈ ደብዳቤ ማህተም ያለዉ ተመልከቱ (“ ሕዚ’ውን እቲ
ብሉፅ መራሒና ብመንፈስ ዝመርሓና ዘሎ ተጋዳላይ መለስ ዜናዊ እዩ ዝብል ጭርሖ” )( ይህ መርጥ መሪያችን
ኣሁንም በመንፈስ እየመራን ያለዉ ታጋይ መለስ ዜናዊ ነዉ መፈክር) ደብዳቤዋ ተያይዛለች ይህ መፈክር
በትግራይ ከኣባይ ወልዱ የክልሉ ኣስተዳዳሪ ጀምሮ እስከ ቀጠና መሪዎች በደብዳቤ በስብሰባ እነድ ትልቅ
መፈክር ተደርጎ ለመቀስቀስ እየተጠቀሙበት ያለ መፈክር ነዉ።

እንግዲህ ይህን ካልኩ ዘንዳ የ.ህ.ዋ.ህ.ት መሪዎችና መዋቅራቸዉ እያሉን ያሉት ጠ/ሚኒስቴር መለስ በህይወታቸዉ
የሚተካቸዉ ሳያገኙ ሞተዋል እሳቸዉ ከሞቱ ቡኋላም ሌላ እሳቸውን እምተካ በሂወት ሁኖ እሚመራ ስለሌለ
ሞተዉ እንደ እየሱስ ክርስቶስ በመንፈስ እየመሩን ካሉን በ ህ.ዋ.ህ.ት ኢ. ህ.ኣ.ዴ.ግ ስር ተደራጅተዉ ያሉ
ኣመራሮች ሃገርን ለመምራት ካልቻሉ ለምን ኣይለቁም ምክንያቱም ከጠ/ሚኒስቴር ሃይለማርያም ደሳለኝ
ጀምረዉ ያሉት መሪዎች ለ40 (50) ኣመት ኣሁንም ጠ/ሚኒስቴር መለስ መሪያችን ነዉ እያሉን ያሉ ጃነሆይም
እኛ 80 ኣመት እንገዛለን ኣጥንታቸዉም 80 ኣመት ይገዛቸዋል ይሉን ነበር።
10

በኔ እምነት ግን የ ህ.ዋ.ህ.ት መሪዎች መስራት ካልቻላችሁ ልቀቁ ብዙ ቅንና ብቁ ምሁራን ኣሉ እናንተም


በእድሜ በኣቅምም በኣካልም ተዳክማችሃል ስልጣናችሁን ለትውልድ ኣስረክባችሁ ኣማካሪ ሁናችሁ ወደ
ቤተክርስትያን ተጠግታችሁ ንስሃ ብትገቡ ኣለበለዚያ የሙታን መናፍስት መሪዎቻችን ናቸዉ እያላችሁ
በየመድረኩ በየብዙሃን መገናኛ የምትናገሩት እያስገመገማችሁ ነው መድረክ ከፍታችሁ ምን እንመስላለን ብላችሁ
ህዝቡን ብተጠይቁት ህዝብም መስተዋት ስለሆነ ይነግራችሃል እባካችሁ ልብ ግዙ እኔ የምገልፅላችሁ በሁሉም
ህዝብ ላይ ያለ ስሜት ነዉ።

ምናልባት በዚህ ላይ ኣስተያየት መስጠቴን በህ.ዋ.ህ.ት መንደር በሚገባ ከተረዱት እርግጠኛ ነኝ ኣስገደ
ጠ/ሚኒስቴር በመሞታቸዉ ተደስተዋል እንደምትሉኝ እርግጠኛ ነኝ። ስለ ጠ/ሚኒስቴር ሞት ግን ከናንተ በላይ እኔ
ኣዝኛለሁ የናንተ ሃዘን ግን ኣርተፍሻል ሃዘን ነዉ። በየውስኪ ቤት ሞቅ ሲላችሁ ታንፀባርቁታላችሁ።
የትግራይ ኣካል ጉዳተኞች ሃብት በመጠቀም መብታቸዉ ተነጠቀ
የትግራይ ኣካል ጉዳተኞች ከህ.ዋ.ህ.ት ጋር ተሰልፈዉ ፀረ ደርግና ሌሎች ሃይሎች በመዋጋት ሻዕቢያን ከደርግ
ጥቃት ለማዳን ሄደዉ ሲዋጉ ኣካላቸዉ የጎደሉ በክልላችን ከ110,000 በላይ ኣካል ጉዳተኞች ኣሉ እነዚህ
ጉዳተኞች በታጋይነት በሰራዊት ተሰልፈዉ በፀረ ደርግ ውጊያ የተጎዱ በከተማና በገጠር ሆነዉ በካድሬነት ህዝብ
ሲያደራጁ የተጎዱ በተለያየ ጊዜ በገበያ በቤታቸዉ በለቅሶ ወዘተ በደርግ ተዋጊ ጀቶች ተደብድበዉ ኣካላቸዉ
የጎደለ ቢያንስ 110,000 ኣካል ጉዳተኞች ኣሉ። ከነዚህ ውስጥ በኣካላቸዉ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዉ ለሊሰሩ
የማይችሉ በሺ የሚቆጠሩ ናቸዉ ከ100 ሺዎቹ ጡረታ የሚያገኙ ከ5000 በታች ናቸዉ።

የቀሩት ኣካል ጉዳተኞች ጡረታና የሆነ ድጎማ ያላገኘ ህክምና የማይደረግላቸዉ ናቸዉ። ለነዚህ ኣካል ጉዳተኞች
መጦርያ በስማቸዉ ህ.ዋ.ሃ.ት ከተማ ከገባበት ቀን ጀምሮ እስከ ኣሁን ባገር ውስጥና በኣለም ኣቀፍ ደረጃ እርዳታ
እየተጠየቀ ብዙ ድጋፍ ተገኝቷል። በተጨማሪም በስማቸዉ ቴሌቶን በማዘጋጀት በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ
ተሰብስቧል ስለነዚህ የጦር ኣካል ጉዳተኞች ጀግኖች እየተባሉ በካሜራ እየተቀረፁ ብዙ ተብሎላቸዋል። ለነዚህ
ኣካል ጉዳተኞች መጦርያ ተብለዉ በስማቸዉ የተቋቋመዉ ብዙ የንግድና ኣነስተኛ ኢንዱስትሪ ተቋማት
ተመስርተዉ ነበር። ለምሳሌ ለትግራይ ኣካል ጉዳተኞች መጦርያ ተብለዉ ብቻ ከ13በላይ የሸቀጣ ሸቀጥ የጅምላ
ማከፋፈያ ነበሩ ኣሉም። ከ60 በላይ ከባድ ተሽከርካሪዎች እያንዳንዳቸዉ 400 ኩንታል ይጭናሉ በመቀሌ
ከ100.000 በላይ ብር የተሰሩ ህንፃዎች የሚከራዩ ኣሉ በኣዲስ ኣበባ ስቴድዮም ኣካባቢ160 ሚሊዮን እጅግ ትልቅ
ህንፃ ከ12 ፎቅ በላይ የታነፀ የሚከራይ ኣላቸዉ። በነዚህ ኣካልጉዳተኞች ስም ህ.ዋ.ሃ.ት ከ1983 ዓ/ም ጀምሮ እስከ
ኣሁን በመቶ ሚሊዮን ዶላር የሚቆጠር ገንዘብ ለምኖ ኣግኝቷል። ከልዑል ራስ መንገሻ የተወረሱ የፈረንጅ
ከብቶችም በነዚህ ኣከል ጉዳተኞች ስም የተያዙ ናቸዉ።

ይህ ካልኩ እነዚህ ኣካል ጉዳተኞች ከነዚህ በቢልዮን የሚቆጠር (የሚገመት) ገንዘብ ኣካል ጉዳተኞች
ተጠቃሚነታቸዉ ምን ያህል ነዉ የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል? በ ህ.ዋ.ሃ.ት ትግል የተጎዱ ኣካል ጉዳተኞች እስከ
ኣሁን የተጠቀሙበት ነገር ቢኖር 70 የሚሆኑ ፍፁም ኣካላቸዉ የተጎዳ መኖርያ ቤት ኣላቸዉ 10 የሚሆኑ
11

መደጎሚያ ገንዘብ ከ1000 ብር የማይበልጥ ተሰጥቷል። የኣካል ጉዳተኞች ለስሙ በማህበር ተደራጅተዉ ተብሎ
ከ4000 የማይበልጡ በማህበሩ ኣሉ የማህበራቸዉ ዋና ኣላማው ለንግድ የቆመ ሳይሆን ለመረዳጃ ለትርፍ ያልቆመ
ድርጅት ነበር። ኣሁን ግን በቢሊዮን የሚቆጠር ሃብት ያለዉ ( ትንሹ ኤፈርት) የኣካል ጉዳተኞች ማህበር
ባለቤትነት የነበረዉ ድርጅት በኣሁኑ ጊዜ በኣቶ ኣስመላሽ ገ/ስላሴ (ኣባይ ነብስ) የኢትዮጵያ ምክር ቤት
(ፓርላማ) የህግ ጉዳይ ኮሚቴ ሊቀመንበር የሆኑት በቦርድ ሊቀመንበርነት የሚመሩት በቦርድ የሚመራ ህገ-

መንግስት በጣሰ መንገድ በህ.ዋ.ሃ.ት ባለንብረትነት የሚታወቀዉ ኤፈርት ኣይነት ተቆጣጣሪ የሌለዉ ህ.ዋ.ሃ.ት
ኪስ እንደሆነዉ ሁሉ የኣስመላሽ ገ/ስላሴ ድርጅትም ኣንድ ኪስ የባለስልጣኞች የህ.ዋ.ሃ.ት ሆነዋል ምክንያቱም
በትግራይ ኣካል ጉዳተኞች የሚያስተዳድሩት
1. የቦርድ ዳይሬክተሮች
1.1 ኣቶ ኣስመላሽ ገ/ስላሴ (ኣባይ ነብስ) ቦርድ ሊቀ መንበር
1.2 ኣቶ ኣፅበሃ የፓርላማ ኣባል ህ.ዋ.ሃ.ት ታጋይ
1.3 ወዲዓላ የ ህ.ዋ.ሃ.ት ታጋይና ካድሬ
1.4 ኣብረሃለይ ባርነባስ የ ህ.ዋ.ሃ.ት ታጋይና ካድሬ
ልብ በሉ ይህ ድርጅት መጀመሪያ መንግስታዊ ያልሆነ ለትርፍ ያልቆመ የመረዳጃ ድርጅት ነበረ ኣሁን ግን
ሁኔታዉ ተቀይሮ ከ4 እስከ 6 ሰዎች በባለቤትነት የያዙት ለንግድ የቆመ ኣካል ማህበር ነዉ የሆነዉ። በትግራይ
ያሉ ኣካል ጉዳተኞች በ ህ.ዋ.ሃ.ት ተሰልፈዉ ለ17 ዓቀመታት የታገሉ ኣካል ጉዳተኞች በኣሁኒ ጊዜ ኑሮኣቸዉ
የተጎሳቆለና የተመሰቃቀለ ሆኖ ለከባድ ችግር ተዳርገዉ ጡረታ ወይም መደጎምያ ህክምና የማያገኙ ዜጎች ሁነዉ
ይገኛሉ። ሰርተዉ ራሳቸውን እንዳይጦሩ ኣቅም የላቸዉም ታዲያ በነ ኣባይ ነብስ በሌለበት የተያዘ የኣካል
ጉዳተኞች ሃብት ምን ሊሆን ነዉ ጉዳይ ሁሉ ለዜጎች ተቆርቋሪ ነኝ ባይ ዜጋ መጠየቅ ኣለበት።

በትግራይ ክልል ይሁን በለሌላ ክልሎች የሚገኙ ኣካል ጉዳተኞች በህ.ዋ.ሃ.ት ፓርቲ ተሰልፈዉ ኣካላቸዉ የጎደሉ
ብቻ ናቸዉ የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል።በኔ እምነት በትግራይ ይሁን በለሌላ ክልሎች የሚገኙ ኣካል ጉዳተኞች
የህ.ዋ.ሃ.ት ብቻ ሳይሆን ከኣፄ ሃ/ስላሴ ጀምረዉ በደርግ ጊዜ በሌሎች ደርግን ተቃዉመዉ በፀረ ደርግ ውጊያ
ኣካላቸዉ የጎደለ ዜጎች እጅግ ብዙ ናቸዉ። በኣላማ ደረጃም ከጃነሆይና ከደርግ ጎን ተሰልፈዉ ኣካላቸዉ የጎደለ
ወታደሮች ምንም እንኳን የነበሩ ስርኣቶች ኣድሃርያን ቢኖሩም እነዛ በወቅቱ ኣካላቸዉ የጎደሉ ወታደሮች
ሉኣላዊነትዋና ኣንድነትዋ የተጠበቀች ኢትዮጵያ እንድትኖር ብለዉ የተዋጉ ነበሩ። ምንም እንኳን ከፀረ
ዲሞክራሲ ስርኣቶች ቢሰለፉ እንደ ዜጎች እኩል ከ ህ.ዋ.ሃ.ት ኣካል ጉዳተኞች እንክብካቤ ያስገልጋቸዋል …..የ
ህ.ዋ.ሃ.ት መንግስት የኢትዮጵያ ሉኣላዊነት ተደፍሮ ኣገራችን እንድትቆራረስ ያደረገ የባህር በር እንድታጣ ያደረገ
ነዉ። የህ.ዋ.ሃ.ት ሰራዊት ጠንካራ ጎኑ ለደርግ ስለተዋጋ ነዉ ስለዚህ በ ህ.ዋ.ሃ.ት ም ሆነ በደርግ ተሰልፈዉ ሲዋጉ
የተጎዱ ዜጎች እኩል መታየት ኣለባቸዉ። ዋናዉ ነገር በኣቶ ኣባይ ነብስ ባለቤትነት የተያዘዉ የትግራይ ኣካል
ጉዳተኞች ሃብት ኣካል ጉዳተኞች በህግ ቢጠይቋቸዉ ለሁሉም በተለያዩ ስሞች የሚጭበረበሩ ሃብት ማካበት
የተያያዙ ማስተማሪያ ይሆናል።
12

እዚህ ላይ ሳልጠቅሰዉ ያለፍኩት ህ.ዋ.ሃ.ት ገንዘብ እሚገኝበት ድርጅቶች ለማቋቋም ትልቅ ችሎታ ነበረዉ ይህም
ቀድም ሲል እንደ ኤፋርት ሬስት ትግራይ ልማት ማህበር ነበሩ ቡኋላም የኣካል ጉዳተኞች ማህበር ኣሁን ወደ
ኣክሲዮን የተቀየረ ኣሁን ደግሞ የታጋዮች የነበረ መረዳጃ ማህበር በሚል በኣቶ ሙሉጌታ ኣለምሰገድ የዛሬዉ
የጣሊያን ኣምባሳደርና በተኽለወይኒ ኣሰፋ ሬስት ዳይሬክር የሚጠራ ተቋቁሟዋል። እነዚህ ሁሉ ማህበራት ገንዘብ
የማግኛ ዘዴ እንጂ ለትግራይ ህዝብ ያመጡለት ፋይዳ የለም። ይህ ሃብት የትግራይ ህዝብ ኣበጥሮ ያውቀዋል
ስለሆነም እባካችሁ ዘመዶቼ ተንኮል ስለማይጠቅም ቀና ነገር እንስራ።

በትግራይ ኣካል ጉዳተኞች በኣሁኑ ጊዜ በተለይ በመቀሌ፣ ኣዲግራት፣ ኣክሱም፣ ሽሬ የሚገኙ በልመና
ተሰማርተዉ ተበላሽተዉ ይገኛሉ። ታዲያ የነኣባይ ነብስ (ኣስመላሽ ገ/ስላሴ) በቢልዮን የሚቆጠር ገንዘብ መቼ
ሊጠቀሙበት ነዉ በደርግ ወገን ተሰልፈዉ ኣካላቸዉ የጎደሉ ዜጎች ጭራሹን ጠያቂ የላቸዉም የነዚህ ዜጎች
ጉዳይም መታየት ያለበት ጉዳይ ነዉ። የኣንድ ኣገር ዜጎች ሆነን እንደ የቤት ልጆችና የውጭ ልጆች ሆነን
መታየት የለብንም እነዚህ የተረሱት የደርግ ነባር ኣካል ጉዳተኞች በትግራይ ያሉት ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያዊ
የሆነ ዜጋ የቻለዉን ነገር እንዲከባከባቸዉ ከተቻለም ኣለም ኣቀፍ እርዳታ ሊጠይቅላቸዉ ይገባል እነዚህ የደርግ
ኣካል ጉዳተኞች ኤርትራ ኢትዮጵያ ናት ኦጋዴን ..ኛ ሉኣላዊ ነዉ ቀይ ባህርየኛ ነዉ የሃገራችን ሉኣላዊነት
ይከበር ሲሉ ነዉ ኣካላቸዉ የጎደለዉ።

መንግስት ከሃይማኖት ጣልቃ ገብነት እጁን ያውጣ


በብዙ ዜጎች መስዋእት የተመሰረተ የሃገራችን ህገ-መንግስት ማንም ዜጋ የፈለገውን እምነት እንዲያራምድ የሚል
ኣንቀፅ በመፅደቁ መንግስት በሃይማኖት ሃይማኖት በመንግስት እጃቸውን ማስገባት የለባቸዉም የሚል ህገ-
መንግስት በሁሉም የሃገራችን ኣማኒያን ተቀበቀይነት ኣግኝቶ ቆይቷል። ሆነም ግን የህ.ዋ.ሃ.ት ኢ.ህ.ኣ.ደ.ግ
ፓርቲና መንግስት ስልጣን ከያዘበት ቀን ጀምሮ ምንም እንኳን እንደ ዛሬ በሙስሊሙ ህብረተሰብ በግዕፅ
በሃይማኖት እጁ ባያስገባም የሃይማኖት በኣላት ለማክበር በሚል ሽፋን የሃይማኖት መድረኮች የፖለቲካ መጫወቻ
ሜዳ ኣደርገዋቸዉ እንደቆዩ ሁሉም ዜጋ ያውቃል።

ይህ በሃይማኖት ጣልቃ መግባት በህ.ዋ.ህ.ት መንደር ለኔ ኣዲስ ኣይደለም ህዝብ ግን በቅን መንገድ እያዩ ዝም
ብሎ ነዉ የቆየዉ ነገር ግን ህ.ዋ.ህ.ት ከጅምሩ ይዞት የመጣዉ ማለሊታዊ ኣቅጣጫ ከትጥቅ ትግል ጀምሮ ሁሉም
የህብረተሰብ ኣስተሳሰብ እምነቶች ባህሎች የህዝብ ጥያቄዎች ማህበራት የሞያ ይሁን የሌላ ኣደረጃጀት ከማለሊት
ኣቅጣጫ ውጭ እንዳይሄዱ በውስጣቸዉ ሰርፆ በመግባት ሁሉም ኣይነት እንቅስቃሴ ወደ ጥቅምህ ቀይረዉ የሚል
እምነት ነበረዉ ይህ ማለት ህ.ዋ.ህ.ት እነዛ የተጠቀሱ ኣካላት ነፃነታቸውን ለማክበር እምቢ ለሞግዘዚትነት
ብለዉ ካፈነገጡ ሊያፍናቸዉ እንደሚችል የሚያመላክት ነዉ። ኣሁን በሙስሊሙና በ ህ.ዋ.ሃ.ት ና ኢ.ህ.ኣ.ደ.ግ
13

ያለ መፋጠጥም ህ.ዋ.ሃ.ት የሃይማኖት እምነት ነፃነት መብት ለማስከበር ቁርጠኝነት ….በውስጡ የነበረ ድብቅ
ኮሚኒስት ኣስተሳሰብ ስለ ኣገረሸበት ነዉ።

የተከበራችሁ ኣንባቢያን የኢትዮጵያ መንግስት በሙስሊሙ ህብረተሰብ ሃይማኖት ጣልቃ በመግባቱ በኣስር
ሚሊዮን በሚቆጠሩ ሙስሊሞችና በመንግስት እየተፈጠረ ያለዉ መፋጠጥ መንግስት በፈጠረዉ በእምነት ጣልቃ
ገብነትና ህግ-መንግስትን መናድ ኣድርጌ ነዉ የምወስደዉ እኔ በሌላ ክልሎች ያሉት በመንግስትና በሙስሊሙ
ህብረተሰብ ያለዉ ጥያቄ ውዝግብ በሩቅ ነዉ እምሰማውና በሚድያ የምከታተለዉ ኣሁን የማተኩርበት ጉዳይ ግን
በትግራይ ያሉት ሙስሊሞች እጅግ ብዙ ናቸዉ እነዚህ ዜጎች ከረጅም ኣመት በፊት በስልጣኔና በንግድ
ከክርስቲያኑ ህብረተሰብ ትንሽ የመጠቁ ስለነበሩ ክርስቲያኑ በሙሉ ለማለት ይቻላል በእርሻ ነበር የሚተዳደረዉ
በዚህ ባለፉት ምእተ ኣመታት በክርስቲያኑና በሙስሊለሙ ህብረተሰብ ገዢዎች በሚፈጥሩት ኣልፎ ኣልፎ
በኣክሱም የሚታየዉ ትንንሽ ግጭት ካዕሆነ ግጭት የሚባል ነገር ኣልነበረም ።

በሁለቱ ሃይማኖቶች ግጭትና ኣለመተማመን ኣይተን ኣናውቅም ጎዞዉ እንደዚህ እያለ በትግራይ ሲደረጉ
የከረሙትንእንመልከት ባለፈዉ ክረምት ከየመስጊዱ የተወከሉ በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ማረፊያ ተሰጥቷቸዉ የቀን
ዉሎ ኣበል ተሰጥቶ ለ13 ቀናት ስብሰባ ተደረገላቸዉ ከዚያ ቡኋላ በሙስሊሙ ህብረተሰብ ማጉረምረም ተጀመረ
ክርስቲያኑም ጥያቄ ማንሳት ጀመረ ቆይቶም መንግስት እሚያደርገዉን ጣልቃገብነት መቃወም ኣሳየ።

የህ.ወ.ሃ.ት ካድሬዎች በቀበሌ በተለያዩ መድፈኮች ወሃብዮ የሚባል የኣልቃይዳ መርበብ ኣምላኪ ኣክራሪዎች
ገብተዋል ህዝበ ክርስቲያን እንደጠላት የሚመለከት ኢትዮጵያ የሙስሊሙ ሃይማኖት የበላይነት የተረጋገጠበት
ኣገር ልትሆን የሚያስቡ በጅሃድ የሚያምኑ ናቸዉ እያሉ ህዝብን ሰብስበዉ ተናግረዋል። በሁሉም ቀበሌዎች
መስሪያ ቤቶች የተሰበሰበ ክርስቲያን ህዝብ ተቃውሟል በቃ ኣበቃ በሙስሊሙና በክርስቲያኑ ሊፈጠር የታሰበዉ
የመቃቃር ዘመቻ ኣልተሳካም ካድሬዎችም ውሃ ዘግነው ቀሩ።ሁሉም ነገር ኣልሆን ብሎ ስላልተሳካላቸዉ
በሙስሊሙ የሃይማኖት ኣይነቶች ወሃቢይ፣ሱኒይ፣ ሽዓ፣ ኣሕባሽ የሚባሉ በሙስሊሙ ህብረተሰብ ቀርበዉ ውይይት
ተደረገ ኣሕባሽ የሚባል ሃይማኖት በኣብዛኛዉ በሙስሊሙ ተቀባይነት ኣጣ። ስለ ኣሕባሽ ማንነት ለማሰልጠን
ጥቂት ኣላማዎችና ሌሎች በሰንዳፋ፣ በሃረር እየሄዱ ይሰለጥኑ ነበር።

በሙስሊሙ ህብረተሰብ ግን በብዙሃኑ ኣንድነት ማላላት ኣይታይም ነበር ከጥቂት ሙስሊሞች ውጭ ሁሉም
ሙስሊም ነባር መጅሊስ ወርዶ በመስጊዳችን የምናምናቸዉ መሪዎች እንምረጥ ነዉ ያሉት።ውስጥ ለውስጥ ግን
በጥቂት ግለሰቦች ሙስሊሙ ህብረተሰብ ታመሰ ከመታመስም ኣልፎ …….. በሙስሊሞች ባልና ሚስትም ግጭት
ተጀመረ ቅስቀሳዉ ቤት ለቤት ነበረ ይህ መታወክ ሙስሊሞች ባሉበት በመላዉ የትግራይ ዞኖች፣ ወረዳ ቀበሌ
14

ነበር በምርጫዉ ወቅት ሲታዩ የነበሩት ቤት የሚውሉ ሽማግሌዎች ሴቶችና ወንዶች ነበሩ ወጣቱና መካከለኛ
እድሜ ያላቸዉ ሙስሊሞች ኣብዛኞቹ ኣልመረጡም ከምርጫ ቡኋላም ሙስሊሙ ህብረተሰብ ደስተኛ ኣልነበረም
ተሰልፎ ኣይናገርም ዝምታ በዝምታ ይህ ኣደገኛ ነገር ነዉ። ህዝብ ኣግራሞት ግራ ያጋባዉ ሙስሊሙ ህብረተሰብ
ለምን ኣስር ወይም ከዛ በላይ ሃይማኖት ኣይፈጥሩም ለምን ህዝበ ክርስቲያን በኢትዮጵያ ከ8 ከዛ በላይ
ሃይማኖቶች ይኖራሉ በሌሎች ኣገሮች እኮ ጥይት ካልተኮሱ ፈንጅ ካልቀበሩ የፈለጉትን ሃይማኖት የሚያመልኩ
በመቶ የሚቆጠሩ ሃይማኖት የሚያምኑ ሰዎች ያሉበት ኣገር ኣለ።

ለምን ኢትዮጵያ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ የወሃብይ ሃይማኖት ተከታዮች ኣሸባሪዎች (የኣሸባሪዎች መርበብ) ፂምህን
ኣረዘምክ ሱሪህን ኣሳጠርክ ይባላሉ በሃገራችን ንቃተ ህሊናችን ዝቅተኛ በነበረበት ለፔንጤና ሌላ ሃይማኖት
ተከታዮች እንጨፈጭፍ ነበር ዛሬ ቤተመንግስትና ሌሎች የመስሪያቤት ስልጣን ይዘዉ ለመምራት በቅቷል በኔ
እምነት የሆነ ሃይማኖት ተከታይ መሪ ቢሆን ትፍጉም ኣይሰጠኝም ታዲያ የህ.ዋ.ሃ.ት ኢ.ህ.ኣ.ደ.ግ መንግስት
በሙስሊሙ ህብረተሰብ ያለ ልዩነት ምን ኣገባው ራሳቸዉ ለምን ኣይፈቱትም ? ከተራበሹ ደግሞ በህግ መንግስቱ
መሰረት ይቀጣሉ ካለበለዚያ የመንግስት ት/ቤቶች ለምን የሃይማኖት መሪዎች ማሰልጠኛ ይሆናሉ? በኔ እምነት
ኣሁንም መንግስት ከሃይማኖት ጣልቃ ገብነት እጁን ያውጣ ፀጥታዉ ያስከብር ህገመንግስት የማያከብሩ የተለያዩ
ሃይማኖት ተከታዮች በህግ ይቀጡ ከዛ ውጭ መሄድ ለመንግስትም ለሙስሊሙ ህብረተሰብ ኣይጠቅምም በትግራይ

ያሉ የሙስሊሙ ህብረተሰብ መጨናነቅ መንግስት ተቀራርቦ በመግባባት መፍታት ኣለበት(በሌላ ክልልም


እንደዚሁ መንግስትም ሙስሊሙም ሌሎች ሃይማኖቶች ህገመንግስቱን ኣክብሩ በተለይ ደግሞ የህ.ዋ.ህ.ት
ኢ.ህ.ኣ.ዴ.ግ መንግስት በሃይማኖት ኣማኒያን መካከል እጁን ያውጣ

የህ.ዋ.ህ.ትኢ.ህ.ኣ.ዴ.ግ መንግስት የመድብለ ፓርቲ መኖርና ዲሞክራሲያዊና ሁሉም ኣቀፍ ኣሳታፊ ምርጫ
እያጨለመዉ ይገኛል።

በኣሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ መንግት የኣካባቢ የወረዳ የቀበሌ ምርጫ ለማካሄድ የህ.ዋ.ህ.ት ኢ.ህ.ኣ.ዴ.ግ ራሱ ብቻ
ባቋቋመዉ ምርጫ ቦርድ ለምርጫ ዝግጅት እየተሸባሸበ ይገኛል። በቅርቡም ተኣስመራጮች ሰሚናር (ስልጠና)
ለመስጠት በመንግስት ብዙሃን መገናኛ እየተናገሩ ሰንብቷል ለስልጠናም በብዙ ሚሊዮን የሚገመት ለወር ኣበልና
መጓጓዧ እንደመደቡ ታውቋል።

ለመሆኑ ህ.ዋ.ህ.ት ኢ.ህ.ኣ.ዴ.ግ የኣካባቢና የወረዳ የቀበሌ ምክር ቤቶች ኣስመርጣለሁ ሲለን ባለፉት 21
ኣመታት እንደተከተለዉ የምርጫ ኣፈፃፀም ሊከተል ነዉ ውይስ በኣሁኑ ጊዜ ያለዉ የኣለም ሁኔታ ተረድታችሁ
15

ያሻሻላችሁት ኣለ ማለት ነዉ? በ1997፣ በ2002 ዓ/ም የነበሩ የምርጫ ሂደቶች ኣፋኝና ፀረ ዲሞክራሲ የምርጫ
ኣቅጣጫና ኣፈፃፀም እንደነበረ መላዉ የኢትዮጵያ ህዝብና ኣለም ኣቀፍ ታዛቢዎች ኣረጋግጠውታል። የነበረዉ
ሁነኔታ ሳይቀቆይ ምርጫ እናካሂዳለን እየተባለ ያለዉ ምን ለመማምጣት ነዉ ? እስኪ ለኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ
እሚገባዉ ከሆነ ያለዉ ሁኔታ ጠቁሜዉ ልለፍ። ይህን ስል ግን ምርጫ ቦርድ ሁኔታዉን ኣይቶ ነገሮችን ተንትኖ
ተረድቶት በራሱ እምነት ነፃ ሁኖ ከ ህ.ዋ.ህ.ት ሞግዚትነት ውጭ ይሰራል የሚል እምነት ስላለኝ ኣይደለም ግን
ህዘቡ ኣውቆት እንዲዘጋጅና ብሎም እንዲታገለዉ ለመጠቆም ነዉ።

ከመለስ ዜናዊ ሞት ተከትሎ ለፖለቲካ ፓርቲ ኣባላት ለመበታተን እየተደረገያለ ስራ ከኣሁን በፊት
እንደገለፅኩት ትግራይን እንደ ሞዴል እንውሰድና ሁሉም ህብረተሰብ በእድሜና በፆታ በመለየት ሁሉም በ
ህ.ዋ.ህ.ት ኔት ዎርክ በኣባልነት እንዲደራጅ ከ ህ.ዋ.ህ.ት ኣባልም ውጭ የሚታመን ሰዉ የለም። 21 ኣመት ሙሉ
ምርጫ ያስፈፀሙ የምርጫ ቦርድ መዋቅር የነበሩና ባለፉት ምርጫዎች ለገዥ ፓርቲ ብቻ ወግነዉ ለተቃዋሚ
ፖለቲካ ፓርቲዎች ብዙ እንግልት የፈፀሙ ናቸዉ። እነዚህ የምርጫ መዋቅር በህ.ዋ.ሃ.ት ብቻ የተዋቀሩ ናቸዉ።
ህ.ዋ.ህ.ት በኣሁኑ ጊዜ በትግራይ ያለዉ ኣረና መድረክ በየከተሞች ፅ/ቤት ከፍቶ እንዳይሰራ የህዝብ ቤት
እንዳይከራይ ህዝቡን በማስፈራራት ተቃዋሚ ፓርቲ በገፅ መሬት እንዳይኖር እያደረገ ይገኛል። የክልል
የመንግስት ሰራተኛም ሆነ ነጋዴ ማህበራት ተማሪዎች በሙሉ 100% የ ህ.ዋ.ህ.ት መሆን ግዴታ ነዉ።

የ ህ.ዋ.ህ.ት ኣባል ያልሆነ የመለስ ራእይ (..) የማይከተል በመለስ መንፈስ የማይመራ የከዳ እየተባለ ነዉ።
የተቃዋሚ ፓርቲ ኣባላት ማህበራዊ ሁኔታቸውን ቀውስ እንዲገባዉ ሆን ተብሎ ህ.ዋ.ህ.ት እየሰራ ነዉ። ይህ እንደ
ማስረጃ ያክል ከኣረና ትግራይ ጋብቻ የፈፀሙ ዜጎች ከኣረና ኣብረዉ እንደ ጠላት የሚታዩበት የኣረና ኣባል
በቤቱ ቀውስ እንዲፈጠር በሚስቱ ቤተሰቦች ተፅእኖ በመፍጠር ሚስቱን ስራ መከልከል ለኣረና ኣባል በተሰቦቹ

ሳይቀሩ ማህበራዊ ኑሮኣቸዉ እንዲበላሽ በማድረግ ለተቃዋሚ ፓርቲ ኣባላት ቤት ኣከራዮች ካከራዩ ተፅእኖ
መፍጠር ጭንቀት በመፍጠር እንደዜጎች እንዳይታዩ በማድረግ ባለበት በዚህ ባለፍነዉ 5 ኣመት ከኣረና ትግራይ
ኣባላት ከ150 በላይ ከትዳራቸዉ ተፋትተዋል ውይም ተሞክረዋል። በሺ የሚቆጠሩ የኣባላት ቤተሰቦች ከብዙ
የስራ እድል የትምህርት እድል ተገልለዋል ሌላዉ ቀርቶ በደርግ በጠበል ብጥምቀት ለኣረና ኣባላት እንዳይጠሩ
የሚሳቀቁበት ኣብረዉ ሻሂ መጠጣት መንገድ ላይ ኣብሮ መሄድ ህብረተሰቡ እየተሸማቀቀ እንዴት ብሎ ምርጫ
ያካሂዳል።

የድህንነት ኣባላይ ለሃገራችን ኣደጋ የሆነ የኢኮኖሚ የማህበራዊ ፣ የሙስና ኣጠቃላይ ኣገራችን ወደ ኣደጋ
የሚዳርግ ወንጀል ለመከላከል እንደመስራት ለተቃዋሚ ፓርቲ ኣባላት በመክበብ በክትትል ወጥመድ ውስጥ
በማስገባት በሚያሰቃዩበት በትግራይ ሊስትሮ፣ የቡና ቤት ሰራተኛ ሳይቀሩ ለስለላ እንዲሰማሩ የተቃዋሚ ፓርቲ
16

ኣባላት ምን ተናገሩ ከማን ጋር ሄዱ በማለት በሁሉም የስለላ ዓይን የተነጣጠረበት ሁኔታ ምርጫ ይካሄዳል ተብሎ
በየትኛዉ መመዘኛ ምርጫ ይፈፀማል።

ነፃነት የህግ የበላይነትና እኩል የህግ ተገልጋይነት በሌለበት ተቃዋሚ ፓርቲ እንደ ዜጋ የማይታይበት ሁኔታ
እያለ የመንግስት ብዙሃን መገናኛ በተቃዋሚዎች ጫንቃ የስድብ ናዳ እያወረደበት ገዥ ፓርቲ የሃገራችንን
የመንግስትና የመንግስት ያልሆኑ ሃብት ለብቻዉ ሟጥጦ እየተጠቀመ ምርጫ ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ይፈፀማል
ማለት እንዴት ይታመናል? ከላይ የዘረዘርኳቸዉ ለምርጫ እንቅፋት የሆኑት ነጥቦች በትግራይ ብቻ የሚፈፀሙ
ችግሮች ኣይደሉም ኣሁንም እነዚህ ስራዎች እነዳሉ ተገላብጠዉ እዳዉ በባሰ መንገድ በኣማራ ፣ በኦሮሞ፣ በደቡብ
በሌሎች ክልሎችም ተፈፅሟል…ስለዚህ የወረዳና የቀበሌ የኣካባቢ ምርጫ ለማስፈፀም ስልጠና ….ማለቱ ኣጃቢ
ብዬዉ ልለፍ በኔ እምነት ህ.ዋ.ህ.ት ኢ.ህ.ኣ.ዴ.ግ ውስጡ ባዶ የሆነ የኢትዮጵያ ኣርትፍሻል ዲሞክራሲ መፈክር
ይዞ ከሚያንሳፍፈን በተጨማሪ ስለዲሞክራሲ ብለዉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወጣቶች በጦርነት ያለቁበት በጎዳና
ተረሽነዉ የተዘረጉበት የታሰሩበት የተገረፉበት በእሳትና በኤሌክትሪክ የተቃጠሉበት ..የተሻለ ተብሎ የፀደቀ
ህገመንግስት እየቀለዱበት ስለሆነ በዚህ ጉዳይ ከመቀለድ ይልቅ ወደኋላ ተመልሶ ጉዞዉን ፈትሾ የሰራቸውን ፀረ
ዲሞክራሲ ስራዎች ሂስ በማድረግ የዜጎችን ነፃነት ተረጋግጦ ሰላማዊ ምርጫ ለማስፈፀም ደግሞ የምርጫ መዋቅር
ኣደረጃጀት ኣመላመል በማሻሻል ይስተካከላል ኣለበለዚያ ኣፋኝ ለሆነ ምርጫ በሃገራችን ኣንጡራ ሃብት ማባከን
ትርጉም የለዉም።

ነፃ ምርጫ ሊፈፀም ከ ሆነ ህ.ዋ.ህ.ት ኢ.ህ.ኣ.ደ.ግ የብሄር የሃይማኖት የዘር የቀለም ልዩነት ሳያደርግ መጀመሪያ
ራሱ በህብረተሰቡ የፈጠረዉ መቃቃር እንዲፈታ ያድርግ ይህ የሚፈታው ህ.ዋ.ህ.ት ከቂም በቀል ተግባር
ሲቆጠብ ነዉ። የፖሊስ፣ ድህንነት ሌሎች የፍትህ ኣካላት ለህ.ዋ.ህ.ት መወገን ኣቁመዉ ለሁሉም ፓርቲዎች
እኩል ማየት ኣለባቸዉ። ኣሁን ያለዉ ምርጫ ቦርድ በኢትዮጵያ በተቃዋሚ ፓርቲዎች ታማኝነት የለዉም በ
ህ.ዋ.ህ.ት መንግስትና በተቃዋሚዎች ተመርጠዉ ይቋቋሙ ካልሆነ የሚመጣዉ ምርጫ ተቃዋሚዎች መሳተፋቸዉ
ኣይታየኝም ህ.ዋ.ህ.ት ኢ.ህ.ኣ.ዴ.ግ ብቻውን ኣጨብጭቦ ቆሞ ይቅር። ከዛ ቡኋላ ኣሁን ያለዉ ትውልድ ስራዉን
መስራቱ ኣይቀርም ይህ ከመሆኑ በፊት ግን የ ህ.ዋ.ህ.ት ኢ.ህ.ኣ.ዴ.ግ መሪዎች በዲሞክራሲ ምርጫ የሚያውቁ
ሃገሮች ሄደዉ ልምድ ቢወስዱ ለዚህም ሩቅ ሳይሄዱ የዘንድሮዉ የኣሜሪካዉ ምርጫ ይበቃል።

Anda mungkin juga menyukai